Message
  • Failed loading XML...

wosene

Comments   

0 #2 Wosene Yefru 2019-01-02 04:09
ለተከበሩ ሊቀ ሊቃውንት ዘውገ ፋንታ
በመጀመሪያ የከበረ ሰላምታዮን አቀርባለሁ። አስተያየትዎን ሳነብና ስረዳ ታላቅ የትምህርት ማዕረግ እንዳለዎት ተረድቺአለሁ፤ ስለዚህ በድፍረት ያለማዕረግ ልጽፍ ስለአልፈለኩ “ሊቀ ሊቃዉንት” ብያለሁ፤ ግን ከዚያ በላይ ከሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ። በአስተያየቱም ላይ “ከፍተኛ አድናቆትዎን” [አድናቆቱ ምን እንደሆነ አይታወቅም] ከአቀረቡ በኋላ እንዲህ ይላሉ፤ “ ከተገነዘብኩት ባልሳሳት ሁለት ቁም ነገሮች አቀራረባችው አመች ወይም ትክክል መሆናቸው አጠራጥሮኛል” ይሉና እነዚህ “ሁለት ቁም ነገሮች” ምን እንደሆኑ ሳይነግሩኝ በሶወስት የተከፈሉ “በሀገር ግንባታ” ላይ ያተኮረ ትንታኔ ይሰጣሉ።

“አንደኛ፡ ሕዝብ ተነጋግሮ ያልወሰነው የሀገር መገንቢያ ሊሆን አይችልም”፤

“ሁለተኛ፡ የሀገር መገንቢያ እንደ ዕቅድ ሆኖ በሞዴል ያልቀረበ ቁንጽል ኃሳብ ነው”፤

“ሶወስተኛ፡ የተነጣጠለ የሀገር መገንቢያ ነው”፤

ከዚህ በላይ ከአንድ እስከ ሶወስት የተጻፉትን ምን ለማለት እንደሆነ ለማወቅ አስፈላጊዉን ጥረት አድርጌአለሁ። ነገር ግን ትችቱ አራማባና ቀቦ ሆነ። የስነ ጽሑፍ ሰው ስለአልሆንኩ ትንትንዎ አልገባ ብሎኝ ይሆናል። ጽህፎዎ ከሌሎች ጸሀፊዎች ለየት ያለና ረቀቅ ያለ ችሎታ እንዳሎዎት ያስታውቃል። ግን የሰጡት ትችት ፈጽሞ ከአቀረብኩት ጽሑፍ ጋር አልገናኝ አለኝ። ምን አልባት የሰጡት አስተያየት አሁን በሚያደርጉት ጥናት ላይ የተመሰረተ ነው ብዮ እገምታለሁ። እዚህ ላይ ጽሑፉን እንደገና ይመልከቱት ብሎ መጠየቅ ውድ የሆነውን ግዜዎን ማባከን ይሆናል፤ ደጋግመውም ቤያነቡት ምንም ለውጥ አያመጣም፤ እርስዎ በጥናት ላይ የተመረኮዘ ልዩ የሆነ ሞዴል ስለአለዎት ለኢትዮጵያ ሕዝብና ደህንነት፤ ብልጽግና፤ በኢኮነሜክና በፖለቲካ ሂደት ላቅ ያለና በቅድሚያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጽንሰ ሃሳቡን በማንነተዎ ስለሜያጽደቀው ከሌሎች ከሚቀርበው ሃሳብ የተሻለ መስሎ ስለሚታዮት ሳይሆን አይቀርም ብዮ እገምታለሁ፤ እዚህ ላይ መልስ መሰጣጠቱ አስፈላጌ አይመስለኝም።

እውነቱን ለመናገር “ሞዴል” ምን ማለት እንደሆነም አላውቅም፤ ስለ ኢኮነሚም ሆነ ስለ አገር “ግንባታ” የማውቀው ነገር የለም፤ ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ለውጥ ሊመጣ ነው ተብሎ ስለተወራ በመደሰት ከዚህም ከዚያም አሰባስቤ ምን አልባት የአገሬ ሰው “መልካም አስተዳደር” እንዲያገኝ የሚረዳ መስሎኝ ሕዝብ እንዲወያይበት የቀረቡ አጀንዳዎች ናቸው። እነሱም ከዚህ እንደሜከተሉት ናችው፡

ስለ ሕገ መንግሥት
ስለ ሕግ የበላይነት
ስለ መልካም አስተዳደር [ዲሞክራሴ]
ስለ ሰብአዌ መበት
ስለ ብሔር ብሔረሰቦች
ስለጎሳ
ስለ ብሔራዌ ቋንቋ”
ስለ ክልል መንግሥት

እነዚህ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት የሕዝብ መወያያ አጀንዳዎች “በግብር ሊውል የማይችል፤ ለውጡን የሚያሰናክል፤ በተጠና ሞዴል ያልተደገፈ ቁንጽል” ነው ከተባለ ምርጫውና ዉሳኔው እርስዎ እንዳሉት የሕዝብ ነው። እንዲያውቁልኝ የምፈልገው በጽሕፉ ላይ እንደዚህ ይሁን የሚል የለበትም። ለሕዝብ የቀረበ አጅንዳ ነው፤ ቃል በገቡበት መሰረት ጥናትዎን በሊቀ ሊቃውንት ዘውገ ፋንታ ስም እንደሚያስነቡብን በተስፋ እጠብቃለሁ። በመጨረሻ ለመጀመሪያው ደብዳቤ የተሰጠውን ትችት ማካፈል እወዳለሁ። አስተያየት ሰጭዉም ልክ እርስዎ እንዳሉት “ጽሑፉ የሚያመለክተው የጸሐፊዉን ጅልነትና ለመለስ ዜና ተላላኪ መሆንን ነው [ሳተናውን የመልከቱ]፤ እንደውነቱ ከሆነ ለተላላኪነትም የምበቃ አይመስለኝም፤ እንደርስዎም ታዋቄ አይደለሁም፤ ለመልካም አስተሳሰበዎ አመሰግናእሁ፤ ብዙ የሚሰሩ ነገሮች ስለአሉ በዚህ ላይ ግዜ ማጥፋቱ እርስዎንም እንደኔ ተላላኪ ያደርገዎታል።

ወሰኔ ይፍሩ
Quote
0 #1 Zewge Fanta 2018-12-31 16:22
ሰላም ፕ/ር ወሰኔ ይፍሩ,
ለኢትዮጵያ መንግሥት ጠ/ም ዶ/ር አቢይ እና ለተለያዩ አካሎች የጻፉትን መልዕክትና የአገር መገንቢያ ሀሳቦች በአድንቆት ተመልክቻለሁ። ጠቃሚነትም አጥብቄ እረዳለሁ። ስለዚህ አድናቆቴ ከፍ ያለ ነው። ከተገነዘብኩት ባልሳሳት ሁለት ቁምነገሮች አቀራረባቸው አመች ወይም ትክክል መሆናቸው አጠራጥሮኛል።
አንደኛ፤ ሕዝብ ተነጋግሮ ያልወሰናቸው የሀገር መገንብያ መሰረተ ሀሳቦች በግለሰብም ይሁን በአንድ ወይም በብዙሀን ፓርቲ መሪዎች ዕቅድ ወይም ምርጫ በግብር የሚውል አይደለም። ይኽ ማለት ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው ከውሳኔ ሲደረስ ከሀገር መገንብያ መሰረተ ዕቅዶች ጋር ተዋህደው ይቀርባሉ። የሀገር ግንባታ ስራ በኒዝህ ጽንሰ ሀሳቦች ላይ ተመስርቶ የሚካሄድ ይሆናል። መልዕክትዎ ዕንቁ ሲሆን ከምግባር እንዲውል አቀራረቡ ያሰናክለዋል። መስሎ ታየኝ።
ሁለተኛው፤ ያቀረቡት አማራጭ ሀሳቦች የሀገር መገንብያ አንድ ዕቅድ ሆኖ በሞዴል መልክ ቢቀርብ ለሕዝብ አማራጭነቱን እንዲረዳ ያደርግ ይሆናል። ምክንያቱም በዚህ አገር መገንብያ ሀሳቦች ላይ የተለያዩ ምርጫወች ወይም ዕቅዶች ስለሚኖሩ ለማመዛዘን ይችላሉ፣ ከዚያም የሁሉን ፍላጎት የሚይዘውን መርጠው እንዲደነገግ ያረጋሉ።
ሶስተኛ፤ የሀገር መገንቢያ የሆኑት (የሚሆኑት) ሀሳቦች ተነጣጥለው የገቡ መሰለኝ። ሀገሪቱ ከብዙ ችግር መውጣት የምትፈልግ ሲሆን፣ የቀረቡት ሀሳቦች ተቆንጥለው መሰለኝ። ኢትዮጵያን ለመገንባት ዕቅድ ሆኖ የሚቀርብ በዚህ ቅጥ መስሎ ስለታየኝ ከተሳሳትኩ እንድስተካከል እየጠየኩ፣ አቀርባለሁ፥
የኢትዮጵያ ሀገር መገንብያዎች፣ በሕዝባዊ ዕድገት፣ በብልጽግና (ኢኮኖሚ ሂደት ምርጫ)፣ በፖለቲካ (አስተዳደር) መሰረተ አቋሞች መልክ ሲሆን አንድ እነዚህን የሚመጥን ፍልስፍና በዕቅድ (ሞዴል) መልክ የሚቀርብ ይሆናል። የዕርስዎ ሀሳቦች በዚህ መልክ ቢቀርቡ ጠቃሚ መሰለኝ።
ይህን ለማለት የተገደድኩት በድፍረት ሳይሆን በዚህ ጉዳይ ላይ ትንሽ ጥናቶችን አድርጌ ስለነበር፣ ህሳቦች በዕቅድ (ሞዴል) መልክ ቢቀርቡ እጅግ ጠቃሚ መስለው ስለታዩኝ ነው። አንድን ቤት ለመገንባት በመጠኑ
መጠገን ወይም ከመሰረቱ በላይ ያለውን መገንባት አስፈላጊነቱ መመርመር
አለበት። በበኩሌ ያለው የሕዝባዊ፣ ብልጽግና እና አስተዳደር እንዳለ መገንባት አለበት ባይ ሲሆን፣ ጥገና ሀሳቦች ፈጽሞ ኢትዮጵያን የሚፈውሱ አይሆኑም የሚል አቋም አለኝ። በዚህ ላይ የማቀርበው አንድ ዕቅድ (ሞዴል) አለ። በቅርቡ ተጠናቆ ይቀርባል።
አካባሪዎ
ዘውገ ፋንታ
Quote

Add comment


Security code
Refresh

Additional information