wosene

Comments   

0 #2 ፈቃዱ 2019-01-02 22:33
ወድጄዋለሁ። ብዙ ግንዛቤና እውቀት አግኝቼበታለሁ። እንደዚህ አገራዊ ጠቀሜታ የያዘ ጥናታዊ የኃሣብ ጽሑፍ ላይ አንባቢው በትእግስት አንብቦ ካልተረዳው ተወያይቶ ቁምነገር ላይ ለመግባባት ከመቸገር አልፎ ጭንቀት ውስጥ ይዘፍቃል። ደግሞም ጨርሶ ማንበቡ ጠቀሜታም አለው፤ የተደከመበትም ነው። ይህን ያህል ተገንዝቦ ሁሉንም የሚያነብ፣ ባለ ጉዳይ ማለትም፤ ለመልካም የሚተች፣ ለጠቅላላው ዕውቀት ፍላጎት፣ ለጥቅሙ የሚቃወም ወይም ቅጥር የኔትወርክ ጦረኛ ነው። ታዲያ ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ የሌሎችን ጨምሮ ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅሙ እንጂ፣ ከዚህ ውጭ ሌሎች ጥናቶችን አግልሎ "ሕግ ተጥሷል " ብሎ ሊነታረክ የተዘጋጀ አይመስለኝም። ለሁሉም ከሁለት እስከ አምስት በሚደርስ ገጾች በክፍል ቢቀርብና በተለይ መጽሃፉ እንዲነበብ ሥራ ቢሥራ መልካም ይመስለኛል። ሁሉም እጅግ ጠቃሚና ወቅታዊ ናቸው።
Quote
0 #1 Zewge Fanta 2018-12-31 16:22
ሰላም ፕ/ር ወሰኔ ይፍሩ,
ለኢትዮጵያ መንግሥት ጠ/ም ዶ/ር አቢይ እና ለተለያዩ አካሎች የጻፉትን መልዕክትና የአገር መገንቢያ ሀሳቦች በአድንቆት ተመልክቻለሁ። ጠቃሚነትም አጥብቄ እረዳለሁ። ስለዚህ አድናቆቴ ከፍ ያለ ነው። ከተገነዘብኩት ባልሳሳት ሁለት ቁምነገሮች አቀራረባቸው አመች ወይም ትክክል መሆናቸው አጠራጥሮኛል።
አንደኛ፤ ሕዝብ ተነጋግሮ ያልወሰናቸው የሀገር መገንብያ መሰረተ ሀሳቦች በግለሰብም ይሁን በአንድ ወይም በብዙሀን ፓርቲ መሪዎች ዕቅድ ወይም ምርጫ በግብር የሚውል አይደለም። ይኽ ማለት ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው ከውሳኔ ሲደረስ ከሀገር መገንብያ መሰረተ ዕቅዶች ጋር ተዋህደው ይቀርባሉ። የሀገር ግንባታ ስራ በኒዝህ ጽንሰ ሀሳቦች ላይ ተመስርቶ የሚካሄድ ይሆናል። መልዕክትዎ ዕንቁ ሲሆን ከምግባር እንዲውል አቀራረቡ ያሰናክለዋል። መስሎ ታየኝ።
ሁለተኛው፤ ያቀረቡት አማራጭ ሀሳቦች የሀገር መገንብያ አንድ ዕቅድ ሆኖ በሞዴል መልክ ቢቀርብ ለሕዝብ አማራጭነቱን እንዲረዳ ያደርግ ይሆናል። ምክንያቱም በዚህ አገር መገንብያ ሀሳቦች ላይ የተለያዩ ምርጫወች ወይም ዕቅዶች ስለሚኖሩ ለማመዛዘን ይችላሉ፣ ከዚያም የሁሉን ፍላጎት የሚይዘውን መርጠው እንዲደነገግ ያረጋሉ።
ሶስተኛ፤ የሀገር መገንቢያ የሆኑት (የሚሆኑት) ሀሳቦች ተነጣጥለው የገቡ መሰለኝ። ሀገሪቱ ከብዙ ችግር መውጣት የምትፈልግ ሲሆን፣ የቀረቡት ሀሳቦች ተቆንጥለው መሰለኝ። ኢትዮጵያን ለመገንባት ዕቅድ ሆኖ የሚቀርብ በዚህ ቅጥ መስሎ ስለታየኝ ከተሳሳትኩ እንድስተካከል እየጠየኩ፣ አቀርባለሁ፥
የኢትዮጵያ ሀገር መገንብያዎች፣ በሕዝባዊ ዕድገት፣ በብልጽግና (ኢኮኖሚ ሂደት ምርጫ)፣ በፖለቲካ (አስተዳደር) መሰረተ አቋሞች መልክ ሲሆን አንድ እነዚህን የሚመጥን ፍልስፍና በዕቅድ (ሞዴል) መልክ የሚቀርብ ይሆናል። የዕርስዎ ሀሳቦች በዚህ መልክ ቢቀርቡ ጠቃሚ መሰለኝ።
ይህን ለማለት የተገደድኩት በድፍረት ሳይሆን በዚህ ጉዳይ ላይ ትንሽ ጥናቶችን አድርጌ ስለነበር፣ ህሳቦች በዕቅድ (ሞዴል) መልክ ቢቀርቡ እጅግ ጠቃሚ መስለው ስለታዩኝ ነው። አንድን ቤት ለመገንባት በመጠኑ
መጠገን ወይም ከመሰረቱ በላይ ያለውን መገንባት አስፈላጊነቱ መመርመር
አለበት። በበኩሌ ያለው የሕዝባዊ፣ ብልጽግና እና አስተዳደር እንዳለ መገንባት አለበት ባይ ሲሆን፣ ጥገና ሀሳቦች ፈጽሞ ኢትዮጵያን የሚፈውሱ አይሆኑም የሚል አቋም አለኝ። በዚህ ላይ የማቀርበው አንድ ዕቅድ (ሞዴል) አለ። በቅርቡ ተጠናቆ ይቀርባል።
አካባሪዎ
ዘውገ ፋንታ
Quote

Add comment


Security code
Refresh

Additional information